• A
 • A
 • A
 • АБВ
 • АБВ
 • АБВ
 • А
 • А
 • А
 • А
 • А
Обычная версия сайта

የጥንታዊ ምሥራቅ፡ የጥንታዊ ግሪክና የጥንታዊ ሮማውያን ተቋም

በብሔራዊ የምርምር ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚ ከፍተኛ ትምህርት ቤት፤ የጥንታዊ ምሥራቅ፡  የጥንታዊ ግሪክና የጥንታዊ ሮማውያን ተቋም
የጥንታዊ ምሥራቅ ትምህርት፡ ጥናትና ምርመራን ያያዘ ፕሮግራም የሚሰጥበት ተቋም ነው። የተቋሙ አሰራር በሚከተሉት ጽንሰ ሐሳቦች ላይ የተመሠረተ ነው።

 

    የጥንታዊ ምሥራቅ፡ የጥንታዊ ግሪክና የጥንታዊ ሮማውያን ቋንቋዎችን፡ ሥነ ጽሑፍንና  ታሪክን አዋቂዎች ተባብረው የሚሰሩበት ተቋም በመኾኑ በተለያዩ ዘርፎች ጥናትና ምርምር ማካሄድ ይችላል።

    በጥንታዊና በዘመናዊ የምሥስራቅ ጥናትና ምርምር መካከል በኹሉም ደረጃዎች ዘርፈ ብዙ ጥናትና ምርምር ያካሄዳል ትምህርትም ይሰጥበታል።

    የተቋሙ ጥናት ብዙ የጥንታዊ ዓለም አገራት ቋንቋዎችና ወጎችን(ልማዶችን)ያቀፈ ነው።

    ትምህርትና የጥናት ሥራዎችን ከሥነ ቋንቋ እስከ ሥነ ባህል የተለያዩ ርእሶችን ያካትታል።

    የትምህርት ሂደትንና የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ያዋሕዳል።

    ከሩሲያና ከዓለም አቀፍ የጥናት ማእከሎች ጋር ተባብሮ ይሰራል።

    ሳይንሳዊ ጽሑፎችን በዘመናዊ ዘዴዎች በመጠቀም ያሰራጫል።

የተቋሙ ዋነኛ አቅጣጫዎች

የተቋሙ ምሁራን አብዛኛውን የጥንታዊ ምሥራቅና የጥንት ግሪክና የጥንት ሮማውያን ክፍለ ዓለምን ሥነ ጽሑፎችንና ሥነ ቋንቋዎችን ያስተምራሉና ያጠናሉ። እነሱም የሚከተሉት ናቸው፥

ቻይና፣ ጃፓን፣ ኮርያ፣ ቭዬትናም፣ ካምቦዲያ፣ ላኦስና፣ ታይላንድ፣ ሞንጎልያና ቲቤት፣ ኢራን፣ ጥንታዊ ህንድ፣ የእስልምና ህንድ እና ፓኪስታን፣ የህንድ ድራዊዳዊ ቋንቋዎችና ባህል፣ ቱርክና ቱርክኛ የሚነገርባቸው የመካከለኛ እስያ አገራት፣ የዓረብ ዓለም፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ፣ ጥንታዊ ሜሰፖታሚያ፣ ብሉይ ኪዳንና የብሉይ ኪዳን ዓለም፣ ክርስቲያናዊ ምሥራቅ፣ የሶሪያና የዘመናዊ አራማዊ ቋንቋዎች ጥናት፣ ጥንታዊ ግሪክና ሮም፣ የጥንታዊ ምሥራቅ አርኪኦሎጂ፣ የሩሲያ ምሥራቅና ደቡባዊ ምሥራቅ አርኪኦሎጂ።

የተቋሙ የጥናት አቅጣጫዎች

 • የጥንታዊ ምሥራቅ ህትመቶችንና ትርጉማዊ ሥራዎችን ምርምርና ጥናትን(በረጅም ጊዜ የምርመራና የህትመት መርሀ ግብር መሠረት “ጥንታዊ ምሥራቅ፡ ቀደምት ግሪክና ሮማውያን በጥንታዊ ሥነ ጽሁፎች ውስጥ”)
 • የጥንታዊና የመካከለኛው ዘመን ምሥራቅ ሥነ ቃል ጥናትን
 • የመካከለኛው ዘመን የምሥራቅ ቅኔያዊ ሥነ ጽሑፎች ጥናትን(በተለይም የኢራን፡ የህንድ፡ የቻይና፡ የጃፓን)
 • የጥንታዊ፡ የመካከለኛና የዘመናዊ የምሥራቅን እንዲሁም የምዕራብ ሀገሮች ባህሎች አመዛዛኛዊ ጥናት ማቅረብን
 • ጥንታዊና ዘመናዊ የምሥራቅና የአፍሪቃ ቋንቋዎችን(የሴማዊ ቋንቋዎች፡ ህንዳዊ—አውሮፓዊ ቋንቋዎች፡ የአልታይ ቋንቋዎች፡ የኢንዶ—ቻይና ቋንቋዎች፡ ሲኖ—ቲቤታዊ ቋንቋዎች)በአዝማድነትና በታሪከ ሚዛን መንገዶች በመጠቀም መግለጽን
 • የምሥራቅ አገራት አፈ ታሪክና እምነቶችን የመስክ ጥናት በማካሄድ ውጤቶችን በጽሑፍና በጥናታዊ ትንታኔ ማቅረብን
 • የምሥራቅና የግሪክ አርኬኦሎጂን ያካትታሉ።

ሕትመቶች

የተቋሙ የጥናትና የምርምር ባለሙያዎች በዓለም አቀፍ ሳይንሳዊ መጽሔቶች ውስጥ (በWeb of Science እና Scopus ዝርዝር ውስጥ ያሉ መጽሔቶችን ጨምሮ) የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች አሉዋቸው። መጻሕፍታቸውም በዓለም ላይ ታዋቂ በኾኑ የሳይንሳዊ ጥናት የሚያትሙ ማተሚያ ቤቶች (Brill, de Gruyter, Oxford University Press) ታትመዋል።

ከተቋሙ ፕሮጀክቶች መካከል ተከታታይና ባለብዙ ጥራዝ የኾነውን Orientalia et Classica የሚባለውን ዓለም አቀፋዊ የጥናትና የምርምር መጽሔትና ታዋቂ ባለሙያዎች ተሳትፎ ያደረጉባቸው በውጭ ሀገሮች አታሚዎች የሚታተሙ ስብስብና አንድ ወጥ ጥናታዊ መጻሕፍትን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። በተጨማሪም ተቋሙ Eisenbrauns ከሚባለው ዓለም አቀፍ አታሚዎች ጋር በመተባበር በWeb of Science እና በScopus ዝርዝር ውስጥ የገባውን Babel und Bibel የሚባለውን መጽሔት ያሳትማል። Gorgias Press ከሚባለው ዓለም አቀፍ ማተሚያ ቤት በመተባበር Journal of Language Relationship የሚባለውን መጽሔት ያሳትማል። እነዚህ መጽሔቶች የሚዘጋጁት በዓለም አቀፍ የአርትዖት ቦርድ ሲኾን አብዛኛዎቹ  ጽሑፎች የሚጻፉት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ነው።

 

የተቋሙ ክፍሎች


ተቋሙ ደረጃ  በደረጃ የሚከተሉትን የትምህርት ፕሮግራሞች ይተገብራል፥

 • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና የጥንታዊ እስራኤል ታሪክ
 • የህንድ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ
 • የኢራን ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ
 • የቻይና ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ
 • የኢንዶ—ቻይናና የደቡብ—ምሥራቅ እስያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ
 • የጃፓን ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ
 • የኮርያ ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ
 • የጥንታዊ ሜሰፖታሚያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ
 • የጥንታዊ ሶርያና የፍልስጤም ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ
 • የኢትዮጵያና የዐረብ ዓለም ሥነ ልሳን
 • የኢትዮጵያና የዐረብ ዓለም ሥነ ልሳን
 • የዓረብ አገራት ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ
 • የህንድ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ (ታሚልኛና ሳንስክሪት)
 • የህንድ እና የእስላማዊ ደቡባዊ እስያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ (ኡርዱና ፋርስኛ)
 • የሞንጎሊያና የቲቤት ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ
 • የቱርክኛ ተናጋሪ ህዝቦች ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ
 • የጥንታዊ ግሪክና የሮም ታሪክ
 • የጥንታዊ ግሪክና የሮማውያን ሥነ ጽሑፍ

 

የተቋሙ የትምህርትና የምርምር ቋንቋዎች

ሱሜርኛ፣ አካድኛ፣ ኡጋሪኛ፣ ፊንቄኛ፣ ዕብራይስጥኛ፣ ጥንታዊ አራምኛ፣ ሶርያኛ፣ ዘመናዊ አራምኛ፣ ሑርኛ፣ ኬጥኛ፣ ግዕዝ፣ ዐረብኛ፣ አማርኛ፣ ትግርኛ፣ ሶቆጥርኛ፣ ሳንስክሪት፣ ፓሊ፣ የመካከለኛ ህንድ ቋንቋዎች፣ የላዳኽ ቋንቋ፣ ታሚልኛ፣ ዘመናዊ ፋርስኛ፣ ጥንታዊ ፋርስኛ፣ ኡርዱ፣ ቻይንኛ፣ ጥንታዊ ቻይንኛ፣ ጃፓንኛ፣ ጥንታዊ ጃፓንኛ፣ የኮርያ ቋንቋ፣ ቭየትናምኛ፣ ታይኛ፣ ላኦስኛ፣ የካምቦዲያ ቋንቋ (ኽሜርኛ)፣ ሞንጎልኛ፣ ቲቤትኛ፣ ቻጋታይኛ፣ ጥንታዊ ቱርክኛ፣ ጥንታዊ የኦስማን መንግስት ቋንቋ፣ ቱርክኛ፣ ጥንታዊ ግሪክኛ፣ ላቲን፣ የአናቶልያ ቋንቋዎች፣ የአልታይ ቋንቋዎች፣ ቶኻርኛ፣ የካውካሱስ ቋንቋዎች፣ ቻይናዊ-ቲቤታዊ ቋንቋዎች፣ አውስትሮ—እስያዊ ቋንቋዎች፣ ድራዊዳዊ ቋንቋዎች፣ ቹኮታዊና—ካምቻታዊ ቋንቋዎች፣ የየኒሴይ ወንዝ ቋንቋዎች፣ የኮይሳን ቋንቋዎች.
 

ጥናታዊ ተግባራት

ከተቋሙ የጥናት አቅጣጫዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፥

 • ጥንታዊ ምሥራቅ፡ የአራም ቋንቋዎች ጥናት፡ የሴማዊ ቋንቋዎች ጥናት፡ የደቡብ ዓረብ ቋንቋዎችና ሥነ ቃል
 • የቋንቋዎች ታሪክዊ አመዛዛኝ ጥናት፡ የቋንቋዎች የሩቅ ዝምድና ጥናት፡ የቋንቋ ዝርያ ግላዊ ሥርአትን ማቀነባበር፡ ዝምድና ያላቸውን ቋንቋዎች በየዓይነታቸው መመደብ
 • የጥንት የግሪክና የሮማውያን ሥነ ልሣንና ታሪክ፡ ቋንቋ፡ ስነ ጽሑፍ፡ አፈ ታሪክ፡ የመንግሥታት እና የህዝቦች ታሪክ
 • መካከለኛ ምሥራቅ በኤሊኒዝም ዘመን (አራተኛው ከፍለ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት እስከ አንደኛው ክፍለ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በኋላ)፡ የሶርያና ፍልስጤም ታሪክ ባህልና ኃይማኖት በጥንዊ ዘመን መጨረሺያና በመካከለኛው ዘመን
 • የህንድ፡ ኢራን፡ ሞንጎልያ፡ ቲቤት ጥንታዊ ጽሑፎች፡ የቡዲዝም ሥነ ጽሑፍ፡ የፋርስ ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ፡ የሞንጎልያ የዘመን ቀመር ጽሑፎች፡ የዘውግ ጉዳዮች ጥናት
 • የሩቅ ምሥራቅና ደቡብ ምስራቃዊ እስያ፡ የቻይና፡ የጃፓን፡ የኮርያ፡ የቭዬትናም፡ የካምቦዲያ፡ የላኦስና ታይላንድ ታሪክና ባህል፡ ቋንቋዎች፡ ሥነ ጽሑፍ፡ ሥነ ቃልና የሕዝባዊ እምነቶች ልማዶች
 • በባህሎች ሁለንተናዊ ግንኙነቶች መካከል አመዛዛኝ ጥናት

 

Нашли опечатку?
Выделите её, нажмите Ctrl+Enter и отправьте нам уведомление. Спасибо за участие!
Сервис предназначен только для отправки сообщений об орфографических и пунктуационных ошибках.